
በረከት ማሞ ከህዳር 01 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን በተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ለመምራት ተመድበው አገልግለዋል። ከመስከረም 2 ቀን 2014 ጀምሮ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ እየሰሩ የሚገኝ ይገኛሉ፡፡ አቶ በረከት በወንጀል ጉዳዮች ምርመራ አመራር፣ ክስ እና ሙግት የዳበረ ልምድ ያላቸው ከመሆኑ በተጨማሪ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ስትራቴጂዎችን፣ ፍኖተ ካርታዎችን እና እቅዶችን በመንደፍ፣ በማስተዳደር እና በመተግበር ረገድ የካበተ ልምድ አላቸው። አቶ በረከት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ዲፓርትመንቶችን ሲመሩ ውጤትን መሰረት ያደረገ በሳል አመራር በመስጠት ይታወቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ አቶ በረከት በጣም ጥሩ የተግባቦት ክህሎት ያላቸው ሲሆን ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር ተግባብቶ የመስራት አቅም ፈጥሮላቸዋል፡፡