4ኛው አገር አቀፍ የፍልሰት ምርምር ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል

4th National Migration Research Conference Underway

አራተኛው አገር አቀፍ የፍልሰት ምርምር ጉባዔ በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ የትብብር ጥምረት እና በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጀነት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

መድረኩ የካቲት 26 እና 27 ቀን 2018 ዓ.ም. “Labour Migration, Development, and Migration Governance in Ethiopia: Evidence, Policy, and Collaborative Action” በሚል መሪ ቃል በጂግጂጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የህግና ፍትሕ አገልገሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ በመደረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት በተለያዩ መስኮች የሚከናወኑ ጥናትና ምርምሮች ለፖሊሲ፣ ለሕግና ለስትራቴጂ ቀረፃዎች ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑን ገልጽው፣ በተለይም በፍልሰት ዙሪያ የሚደረጉ ጥናቶች መደበኛ ፍልሰትን ለማበረታታትና መደበኛ ያልሆን ፍልሰትን ለመከላከል የሚያግዙ የሕግ፣ የፖሊሲና የአደረጃጀት ማዕቀፎችን ለመዘርጋት አስፈላጊ መሠረት የሚጥሉ ናቸው ብለዋል።

አክለውም በሀገራችን እስካሁን የተካሄዱ ጥናቶች የተበታተኑ በመሆናቸው በፍልሰት አስተዳደር ላይ የሚጠበቀውን በጎ ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ማሳየት አልቻሉም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም ምክንያት የፍልሰት የምርምር ስራ ቡድን ተጠናክሮ ጥናቶችን በአንድ ቋት ለማደራጀት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት ለመፍጠር እና የሚመነጩ የጥናት ግኝቶች ለፖሊሲ መነሻ እንዲሆኑ መስራት ይኖረበታል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የሶማሌ ክልል የካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን ቃሲም፣ የጅግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰዓድ አህመድነ ጨምሮ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ከ17 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ የምርምር ተቋማት፣ የዓለም አቀፍና የአገር በቀል ድርጅቶችና የግሉ ዘርፍ ተወካዮችም ታድመዋል።

የምርምር ጉባዔው በትብብር ጥምረት ሴከሬታሪያት አነሳሸነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የቆየ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ጉባዔ በዋቸሞ፣ ሁለተኛው በአዲስ አበባ፣ ሶስተኛው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተካሂደዋል፡፡

Tagged Under: act action conference decree development Evidence governance labor labour law legislation Migration migration governance Migration Research National Policy proclamation ratio Regulation res Research Research Conference sea search statute way
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች