ቅርሶችን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ማስወጣት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና ባለቤትነት ማዞርን ለመከላከል እ·ኤ·አ ኖቨምበር 14 ቀን 1970 በፖሪስ የተደረገውን ስምምነት በኢት ዮጵያ ማጽደቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ ባህላዊ ቅርሶችን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው በመሆኑ፤
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጥቅምት 17 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•