የተባበሩት መንግሥታት የመንገድ ትራፊክ ኮንቬንሽን በኦስትሪያ /ቪየና/ እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 7 እስከ ኖቬምበር 8 ቀን1968 ድረስ በተደረገው ውይይት በተሳታፊ አባል ሀገራት የጋራ ውሳኔ ጸድቆ ስራ ላይ የዋለ በመሆኑ፤
ስምምነቱ ዓለም አቀፍ የመንገድ ትራፊክን በሚመለከት የተጠቃለለና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን ድንጋጌዎች የያዘ በመሆኑ፤
ኢትዮጵያ ሀገራችን የባህር በር የሌላት በመሆኗ የመንገድ ትራፊክ ሕጎቿን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማጣጣም ወደ ሌሎች በተለይም ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚደረግን እንቅስቃሴ ቀላልና ቀልጣፋ ለማድረግ እና በሀገራችን ያለውን የመንገድ ደህንነት ከፍ ወዳለ ደረጃ በማሳደግ በመንገድ ትራፊክ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ስምምነቱ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ስለታመነበት፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ልዩ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(12) መሠረት
የሚከተለው ታውጀል፡፡
•
•
•
•