በአገልግሎት ላይ

የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ

ኢትዮጵያ ለስደተኞች መጠጊያና ከለላን የምትሰጥ እንዲሁም ሁኔታዎች በፈቀዱ ጊዜ ላሉባቸው ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የምታበረታታ በመሆኑ፤

ኢትዮጵያ ሰደተኞችን በተመለከተ ተቀብላ ያፀደቀቻቸው ዓለማቀፋዊ ስምምነቶች መኖራቸውና የሃገሪቱ የህግ አካል ማድረጓ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የፀደቀው የአፍሪካ ሰደተኞችን ችግር የተወሰኑ ገፅታዎች የሚገዛው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ኮንቬንሽን አባል በመሆኗ፤

ከላይ በተጠቀሱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ የተቀመጡ መብቶችን የያዘ፣ ለስደተኞች የተሻለ ከለላ የሚሰጥና ለችግሮቻቸው ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል በዓለም አቀፍ መመዘኛዎች መሰረት የተቀረጸ የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፤

የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 409/1996  ጥቅል የሆነና ያልተዘረዘረ ከመሆኑም በላይ በአሁኑ ወቅት ስደተኞችን አስመልክቶ ያለውን አጠቃላይ ለውጥና አዳጊ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ የአገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን የስደተኞችን አያያዝ ለማሻሻል እንዲያስችል የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን እንደገና ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1110/2011
ቀን: የካቲት 20፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1301/2016

ታህሳስ 10፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ