በቅርቡ ፍትህ ሚኒስቴር ለተቀላቀሉ ዐቃቤያነ ህግ ለአምስት ቀናት ሲሰጥ የነበው ተግባር ተኮር ስልጠና ተጠናቀቀ

Task-Oriented Training for Newly Joined Prosecutors at the Ministry of Justice Concludes After Five Days

በ2015 እና በ2016 በጀት ዓመት ለተሾሙ ዐቃቤያነ ሕግ በንቃተ ሕግ : ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ተግባር ተኮር በሆነ ሁኔታ የወንጀል ምርመራ ፣ ክስ ዝግጅት እና ችሎት ክርክር ላይ ያተኮረው የ1ኛ ዙር ሥልጠና በትላትናው እለት ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው የመዝግያ ንግግር እና የሰራ አመራር የሰጡት የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን ሰልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን እውቀት እና ክህሎት በጥብቅ ስነ-ምግባር ስራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የ2ኛ ዙር ሥልጠና በሚቀጥለው ሳምንት በተመሳሳይ መልክ እንደሚሰጥ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Criminal Investigation • Legal Education • Prosecutor training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች