የሀገር አቀፍ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የፌደራል እና ክልል የዳኝነት አካላት፣ የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች አፈጻጸም ተገመገመ

Nine-Month Performance Review of Federal and Regional Judicial Bodies, Ministry of Justice, and Regional Justice Bureaus for the 2017 Ethiopian Fiscal Year's National Justice Transformation

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቢሾፍቱ ከተማ ባዘጋጀው መድረክ የሀገር አቀፍ የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን የ2017ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የፌደራል እና ክልል የዳኝነት አካላት፣ የፍትሕ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች/ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮዎች/ አፈጻጸም በአፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ መሪነት ተግምግሟል።

በመድረኩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት የሀገር አቀፍ የዳኝነት አካሉን ፍኖተ ካርታ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ከማረጋገጥ አንፃር፣ የዳኝነት አገልግሎት ጥራት ፣ቅልጥፍና፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ሌሎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩት ሥራዎችን በመድረኩ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል የፍትሕ አካላትን የትራንስፎርሜሽን የ2017ዓ.ም የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ያቀረቡት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ሲሆኑ፣ በሪፖርታቸውም በመሠረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት ዙሪያ ሰፋፊ ሥራዎች መሰራታቸውን፣ የአስተዳደር ፍትሕ ሥነስርዓትን በክልሎች እንዲተገበር ከማድረግ አንጻር በተሰራው ሥራ ውጤቶች መመዝገባቸውን፣ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ሥራዎች መከናወናቸውን፣በወንጀል ፍትሕ አስተዳደሩም መልካም ጅምሮች መመዝገብ መጀመሩን፣ የፌደራል-ክልሎች ቅንጅታዊ አሠራር እያደገ በመምጣቱ የጋራ ሀገራዊ ሪፖርት ማቀረብ መቻሉ፣ የፍትሕ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ጥረቶች መደረጋቸውን፣ የፍትሕ ዘርፉን ሳቢ ለማድረግ እንዲሁም ምቹ የሥራ ቦታ ለመፍጠር ትላልቅ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ አክለው በባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮችን ሲገልጹ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር ማኔጅመንት እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያልተቋረጠ ክትትል ማድረጋቸው፤ በአንዳንድ አምዶች ሥር መሠረታዊ ለውጥ ያመጡ ሥራዎች መሠራታቸው (መሠረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ፣ የአስተዳደር ፍትሕ፣ የፌደራል-ክልሎች ቅንጅታዊ አሠራርና የጋራ ሪፖርት)፣ ከአጋር አካላት ጋር በመሥራት ሀብት ለማሰባሰብ ጥረት መደረጉ፤ በየሩብ አመቱ የክልሎችን አፈፃፀም ሳይቆራረጥ መገምገም፣ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን በጥንካሬ አንስተዋል።

በሌላ በኩል ብዙ ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ አለመጠናቀቃቸው፤ ወደኋላ የቀሩ አምዶች መኖራቸው (ማጥራት፣ ነጻ የሕግ ድጋፍ፣ አማራጭ የሙግት መፍቻ፣ ተደራሽነት፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ)፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ውሱንነትን እንደ ክፍተት ተነስተዋል።

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይቶች ተደርጎ ግብረመልሶች ከተሰጡ በኃላ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በቀሪ ጊዜያት ትኩረት ተሰጥቶ መከናወን የሚገባቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ እና መመሪያ ሰጥተዋል።

የተከበሩ አፈጉባኤው በሰጡት አቅጣጫ ወደኋላ የቀሩ አምዶችን በልዩ ትኩረት ማከናወን፣የዘገዩ ተግባራትን በማካካሻ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ማከናወን ፣የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ማጠናከር፣የቅንጅት ጥረት ማጠናከር እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

Tagged Under: Access to Justice • Alternative Dispute Resolution • attorney • Attorney General’s Office • bureaus • court • Ethiopian Justice System • federal • Federal High Court • general's • high • house of peoples’ representatives • judicial • Justice • Justice Sector Reform • Legal Aid • legislative oversight • national justice transformation • performance • Performance Evaluation • Regional • Regional Justice Bureaus • review • Rule of Law • Stakeholder Engagement • system • technology in justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች