በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐ/ህግ ዘርፍ የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

FDRE Ministry of Justice Attorney General Sector Hawassa Branch Office Conducted Performance Review

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ታደሰ እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች በተገኙበት የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመትን ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግመዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አሚን አደም የ2017 ዓ/ም የጽህፈት ቤቱን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና ግቦች አፈጻጸም፣ በዕቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተለዩ ጥንካሬዎች እና ውስንነቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ በቀረበው ሪፖርት ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡን በማንሳት በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን በመግለጽ ቀሪ ስራዎችን ጽህፈት ቤቱ እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ስራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ግዜያት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በማሳካት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በተያያዘም ሀዋሳ ከሚገኙ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት ቅንጅታዊ ሥራው ያለበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የምርመራ መዛግብት አፈፃፀም፣ የምስክሮችና ተከሳሾች አቀራረብ እና ተያይዥ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ መስተካከል ያሉባቸውን ጉዳዮች በመለየት ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: attorney • Attorney General • Budget • budget year • case management • customs commission • democratic • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • federal police commission • general • hawassa • Implementation • Legal Proceedings • office • office performance • performance • Performance Evaluation • Performance Review • plan • plan implementation • republic • review • Stakeholder Collaboration • year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች