
አብርሃም አያሌው የብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ሴክሬታሪያትን ከጥቅምት 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመምራት ላይ ይገኛል፡፡
በእርሱ አመራር የሥራ ክፍሉ የትብብር ጥምረቱን የመደገፍና የማስተባበር ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ለማድረግ የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም በፖሊሲና በሕግ፣ በጥምረቱ የአደረጃጀትና የሰራር እንዲሁም የተጠያቂነት ስርዓት ላይ፤ በክልሎች ድጋፍ፣ በስርዓት ግንባታና በዳታ ቤዞች ልማት ላይ በማተኮር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
አብርሃም ከዚህ ቀደም በተለይ በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳ/ጀ በዐቃቤ ሕግነት፣ በአገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች አስተባባሪነት፣ ከሰሜኑ ጦርነት ማግስት በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተቋቋሙ ስምንት የምርመራ ቡድኖችን በበላይነት በማስተባበርና በመምራት የሰራ ሲሆን፤ በቆይታውም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲሁም በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመመርመርና ከሶ በመከራከር የካበተ ልምድ አካብቷል። ከዚህም በኋላ የመንግስት ሕግና ፍትህ አገ/ዘ/ሚ/ዴኤታ አማካሪ በመሆን ያገለገለ ሲሆን፤ አሁን ባለበት የኃላፊነት ደረጃም እነዚህን የቀደሙ ልምዶች በመጠቀም በአገራችን የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር ስርዓት እንዲገነባ በተለይም በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል የማስተባበር ሚናውን በትጋት ለመፈጸም ዝግጁ ነው፡፡