የክልል ጉዳዮች ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት

የክልል ጉዳዮች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች አሉት፡፡ በዚህም መሠረት ዳይሬክቶሬቱ የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የሥራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ በክልሎች በውክልና ለሚታዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ የሚሆን በጀት ድጋፍ እንዲደረግ ያደርጋል፣ ለስራዉ አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነት ይፈጥራል፣ በክልሎች በውክልና የታዩ የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች ላይ የሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራ ያከናውናል፣ በግኝቶቹ መሠረት አስፈላጊው ማስተካከያ እንዲወሰድ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ቅንጅታዊ አሠራርን ለማጠናከር የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ መድረኮች እንዲዘጋጁ ያመቻቻል፣ የዉሳኔ አፈጻጸም ወጥነት እና ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሥልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ሥልጠና ይሰጣል፣ ልምድ ልዉዉጥ በማድረግ ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ በውክልና የተሰጡ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ እና በሰበር የሚታዩ ጉዳዮችን ይከታተላል፣፡

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

No data was found