
ኖህ ታከለ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬትን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ኖህ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የሕግ ባለሙያ ሲሆኑ በዐቃቤ ሕግነት እና በፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ላይ ጥሩ ልምድ ያላቸው አመራር ናቸው። አሁን ካላቸው የሥራ ድርሻ በፊትም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከወረዳ ፍትሕ ቢሮ ጀምሮ እስከ ክልል ፍትሕ ቢሮ ድረስ በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል። ኖህ ፍትሕን ለማስፈን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረጉት ጥረቶች ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
በሥልጠና እና በአቅም ግንባታ ረገድም ኖህ አምስት ዓመታትን በኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት በአሰልጣኝነት ያሳለፉ ሲሆን ሙያዊ እውቀታቸውን ለወጣት የሕግ ባለሙያዎች ማስተላለፍ ችለዋል።
በዚህ ሚናው በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ አዎንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል። ካለበት ኃላፊነት አንፃር የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማነት፣ ግልጸኝነት እና ተደራሽነት ለማሻሻል እስትራቴጅክ ስልቶችን ማዘጋጀት እና እንዲተግበር ማስቻል ይጠበቅበታል።