
መዝሙር ያሬድ የፍትሕ ሚኒስቴርን ከግንቦት 2008 ዓ.ም ጀምሮ የተቀላቀለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጽህፈት ቤት በመምራት ላይ ይገኛል። በዘርፉ ስር የሚገኙ የስራ ክፍሎች ዘርፉን የተመለከቱ የተቋሙን ዕቅዶች እንዲያሳኩ በመደገፍና በመከታተል አስተዋፅኦ አበርክቷል። መዝሙር ያሬድ በማስተባበር ክህሎቱ፣ በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አብሮ በመስራት ስኬታማ ነው። አሁን ካለበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ በተለያዩ ደረጃዎችና ተቋማት ባለሙያና አመራር በመሆን በተለያዩ ደረጃዎች አገልግሏል፡፡ በቴክኖሎጂ ህግ እና በአለም አቀፍ ህግ ተጨማሪ ፍላጎት አለው፡፡ ከ23 አመት በላይ ያካበተውን የስራ ልምድ በመጠቀም ፍትሕን ለማስፈን እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ዘርፉን ለማሻሻልና ለመለወጥ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ ነው።