የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የተቋሙን የ2016 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን እና የ2017 እቅድን የጋራ የማድረግ መድረክ አካሄደ

FDRE Ministry of Justice Conducts Forum to Share the Institution's 2016 Budget Year Performance Report and 2017 Plan

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትሩን ክቡር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ጨምሮ፣ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የተቋሙ መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ቡድን መሪዎች በተገኙበት በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የስትራቴጅክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር የሆኑት አቶ ደሳለኝ መንግስቴ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 እቅድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በበጀት አመቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ከቀረቡ 228‚524 የምርመራ መዛግብት ውሰጥ ለ206‚548 መዝገቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ውሳኔዎችን የሰጠ መሆኑ ተገልፆል። በአገር አቀፍ ደረጃ ክርክር ከተደረገባቸው 198‚178 መዛግብት ውስጥ ደግሞ 111,906 መዝገቦች በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 107,370 መዝገቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በተያያዘ ከሕግ ማርቀቅ ስራዎችን በተመለከተ በአገር አቀፍ ደረጃ 496 ህጎች የተረቀቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል13 በፍትሕ ሚኒስቴር የተቀሩት በክልሎች የተረቀቁ ሲሆን በተጨማሪም በፍትሕ ሚኒስቴር ለ184 የሕግ እርማት ስራ ተሰርቷል።

የመንግሥትና የሕዝብ የፍትሀብሔር ጥቅምን የማስጠበቅ ተግባር ጋር በተገናኘ ክርክር ከተደረገባቸው 26‚834 መዛግብት በገንዘብ መጠናቸው 35,364,591,927.57 እና 17,600,000 የአሜሪካን ዶላር መዛግብት ላይ ክርክር ማድረግ ተችሏል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቡቱ ድርድር ከተደረገባቸው 63 ጉዳዩች እና በክልሎች 2‚699 ጉዳዩች በድርድር ስምምነት በማጠናቀቅ የመንግሥት ተቋማት ሊከፍሉት ይችሉ የነበረ 6.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላርና 199,070,851.33 ብር እንዳይወጣ ማዳን ተችሏል፡፡

ከፌዴራል ህጎች ተፈፃሚነት ጋር በተገናኘ ከተለያዩ አስተዳደር ተቋማት የተላኩ እና የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅን መስፈርት ያሟሉ 51 መመሪያዎች ተመዝግበው በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ ተደራሽ እንዲሆኑ የተደረጉ ሲሆን ፣ ከሰብዓዊ መብት ስራዎች ጋር በተገናኘም 68‚859 ተጠርጣሪ እስረኞችን በመጎብኘት ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዩች እንዲስተካከሉ ተደርጓል።

ህገወጥ የሰዎች ዝርዝር ጋር በተገናኘ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ ክርክር ተደርጎ እስከ 15 ዓመትና ከዚያ በላይ ቅጣት እንዲያገኙ ተደርጓል።

ሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀልን በተመለከተበፍትሕ ሚኒስቴር በ896 መዝገቦች፣ በክልሎች ፍትሕ ቢሮ 8,465 መዛግብት እና ፣በውክልና የተሰሩ የፌዴራል ጉዳዮች በድምሩ 9,361 መዛግብት ላይ ምርመራቸው ተጠናቆ ለዐ/ሕግ ከደረሱት ውስጥ 8,371 መዝገቦች ዉሳኔ አግኝተዋል።

በወንጀል ተግባር በሀገር ውስጥ ሀብት በማጥናት የማሳገድ ተግባራትን በተመለከተ የፍትሕ ሚኒስቴር በ254 ጉዳዮች የፍርድ ቤት እግድ የተሰጠባቸው ጉዳዮች በገንዘብ 1,574,052,588.02 ብር፣2‚727.1 ዶላር፣የአክሲዮን ግምት ብር 152,079,184፣ ቤት ብዛት 204 ቤቶቸ እና 1 ጅ+4 ሕንጻ፣ተሸከርካሪ ብዛት 184፣ማሽነሪ 06 እና መሬት 192,320.27 ካ.ሜ. በበጀት አመቱ ማሳገድ የተቻለ ሲሆን፣ ከወንጀል የተገኘ ሀብትና ንብረትን በተመለከተ ደግሞ12,321,289,473.27ብር ለመንግሰት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል።

ተቋሙ በ2017 የበጀት ዓመትም አምስት መሠረታዊ ግቦችን አንግቦ እንዲሁም በስሩ በርካታ ንኡሳን ተግባራትን በማካተት ከሶስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የተቀዳና ወቅታዊ ጉዳዩች የሚካተቱበትን ስትራቴጂካዊ እቅድ በመያዝ የጋራ እንዲሆን ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

Tagged Under: 2016 • 2016 budget year • 2017 • Anti-Corruption • Asset Recovery • Budget • Budget Execution • case • case management • civil liberties • court decisions • Criminal Justice • democratic • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • fundamental rights • Human Rights • Law Drafting • Legal Proceedings • Legal Reforms • performance • Performance Report • plan • report • republic • strategic • strategic plan • year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች