በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራን በማከናወን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን የማዘመን ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው

በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራን በማከናወን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን የማዘመን ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው•Efforts are Underway to Modernize the Criminal Justice System by Implementing Technology-Backed Operations

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የመረጃ ምዝገባና አስተዳደር ስርዓትን(CAWC-CRIMS) ለመተግበር የሚያግዙና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ድጋፍ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም አድርጓል፡፡

የግብዓቶቹ ድጋፍ ርክክብ በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሉን መረጃ አያያዝ ስርዓታት ላይ የመዋቅር ለውጥ ማድረግ ስለሚያስፈልግ ተቋማት ተቀራርበው በጋራ ሥራቸውን ማከናወን የሚችሉበትን ከባቢያዊ ሁኔታ መፍጠር ስለሚገባ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል እና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ተደራጅቶ የሚመለከታቸው አካላት በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚያደርግ ሲስተም መሆኑ የተጠቅሷል፡፡

ከጥቆማ ጀምሮ እስከ ምርመራና ክስ ያሉ ሂደቶችን አጠቃላይ መረጃ አደራጅቶ መያዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂን መጠቀም መቻል የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ለውጥ የሚፈጥር ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር እና በድሬ ደዋ ዩኒቨርስቲና ሌሎች አጋር አካላት ትብብር መልማት የቻለው በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የመረጃ ምዝገባና አስተዳደር ሥርዓትን(CAWC-CRIMS) የሚፈለገውን አይነት መረጃ መያዝ ከማስቻሉ በተጨማሪ ክትትል ለማድረግ ብሎም የመዛግብት ደህንነትን ለማረጋገጥ የአንድል ወንጀል ሁኔታ ከጥቆማ ጀምሮ አጠቃላይ ሂደቱን አጠናክሮ መረጃን መያዝ የሚያስችል በመሆኑ ከምርመራ አንጻር አጠቃላይ ሥራውን በአጭር ጊዜና በውሱን የሠው ሀይል ማከናወን የሚያስችል ነው፡፡

በመርሃ-ግብሩ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች አጠቃላይ መረጃን ማጠናከር የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅምን አሟጦ በመጠቀም የወንጀል መከላከል ሥራውን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፣ የለማው ሲስተምም በዋነኛነት በአዲስ አበባ ውስጥ በሁለት ክፍለ ከተሞች ለሙከራ ተግባር ላይ እንዲውል የተደረገ እንደሆነና በቀጣይም በሁሉም ክፍለ ከተሞች የከፍ ሲልም አገራዊ አተገባበር እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር የተማከለና ዲጂታል የፍትሕ ሥርአትን እውን ለማድረግ ባቀደው መሰረት በአጠቃላይ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መረጃ በሚመለከት የምርመራ እና የክስ ስርዓቱን መምራት የሚያስችል ዘመኑን የሚመጠን ቴክኖሎጂ በመተግበር ዲጂታላይዜሽንን የሚጠቀም የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child charge Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) Crime criminal Criminal Justice criminal justice administration criminal justice cooperation criminal justice policy criminal justice reform Criminal Justice System crims ethiopian federal justice system Ethiopian Justice System illegal act Justice Justice System offense operation operations per ratio system Technology un violation way
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች