የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የመዝገብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የመዝገብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን፣ የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ ያዘጋጃል ሲፀድቅ ያስተገብራል፤ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት፣ የሀርድዌርና የሶፍትዌር ፍላጎት ያጠናል፣ ስፔሲፊኬሽን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፣ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በአግባቡ መተግብራቸውን ይከታተላል፡፡ የተተገበሩ ሥርዓቶችና መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አገልግሎት መስጠታቸውን ይከታተላል፣ ለሚያጋጥሙ ብልሽቶች የጥገና አገልግሎት ይሰጣል፣ እንዲጠገኑ ያደርጋል፣ ለተጠቃሚዎች የአጠቃቀም ድጋፍና ምክር ያደርጋል፡፡ በተቋሙ ውስጥ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ይዘረጋል፣ ኔትወርክና ሥርዓቶችን ያስተዳድራል፡፡ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን ክትትል ያደርጋል፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ፀጋዬ አማረ ግዛው

ዳይሬክተር