በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም በፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ለሚያልፉ ሕጻናት ጥበቃ የተቋቋመው ብሔራዊ አስተባባሪ ጽ/ቤት የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች ይፈጽማል፡፡ በዚህም መሠረት የብሔራዊ አስተባባሪ አካሉን ስትራቴጂክ እቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ የፍትሕና እንክብካቤ ማእከላት እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ የሴቶችና ህጻናት ምርመራና ክርክር ቡድኖችን እና ስነልቦና ባለሞያዎች ድጋፍ ይሰጣል፣ በሕፃናት ላይ የሚፈፀሙና ከሴቶች ጾታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የመረጃ ስርዓት ያደራጃል፣ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአካል ጉዳተኞች ጉዳዮች በሚቀረፁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎች እና በዕቅዶች ተካተው እንዲፈፀሙ ስርዓት ይቀርፃል፣ መካተታቸውን ያረጋግጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡ የስርአተ ጾታ ኦዲት ያከናውናል፣ የኦዲት ግኝቱ ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፣ ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዩች ዙሪያ ከሚሰሩ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡