የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኩዌት መንግሥት መካከል እኤአ ኦክቶበር 26 ቀን 1998 ኩዌት ላይ በመፈረሙ፣
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው ተዋዋዮቹ አገሮች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መዋዋልና ተፈጻሚ ማድረግን በተመለከተ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቶቻቸው መፈጸማቸውን በዲፕሎማቲክ መስመሮች በመጨረሻ ከተገላለጹበት ወር የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 2 ቀን 1991 ዓ ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•