የኢትዮጵያ መንግሥት ዋና ዋና ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሰነዶችን የተቀበለ በመሆኑ፤
በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች የኢትዮጵያ መንግሥት የሚደግፍ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 25 ቀን 1990 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብቶች ቻርተርን የተቀበለው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•