በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በማሌዥያ መንግሥት መካከል የተደረገው የንግድ ስምምነት ጥቅምት 12 ቀን 1991 ዓም ኩዋላ ላምፑር ላይ የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ከተፈ ረመና በየሕጐቻቸው መሠረትም መሟላት ያለባቸው ሕጋዊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ከተገላለጹ በኋላ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ ስለተመለከተ ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 25 ቀን 1991 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፣
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•