የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበትና የመንግስት ባለስልጣን ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን በመመልከቱ፤
የመንግስት አስፈጻሚ አካላት የሚያከናውኗቸው ተግባራት ከዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር ያላቸው ቁርኝት ከመብታቸው ጋር በተሳሰረ ሁኔታ የሚኖራቸው የወሳኝነት ሥልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመምጣቱና የአስፈጻሚ አካላት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች ወሰን ውጪ ያላለፈ መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
የአስተዳደር በደል እንዳይፈጸም አስቀድሞ በመከላከል ወይም ተፈጽሞ ሲገኝ በአፋጣኝ እንዲታረም በማድረግ በሀገራችን የመልካም የአስተዳደር ሥርዓትን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ስኬታማ የሚሆነው ተቋማዊ የአሠራር ነጻነቱ የተረጋገጠ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ሲኖር መሆኑን በመረዳት፤
በአስፈጻሚ አካላት የሚፈጸሙ የአስተዳደር በደሎች ወይም የሕግ ጥሰቶች እንዲታረሙ በተቋሙ የሚሰጥ የመፍትሔ ሐሳብ ለማስፈጸም መሰናክል የነበረን ክፍተት በማስወገድ በምርመራ እና ቁጥጥር ሥራዎቻችን ያዳበርናቸውን አዎንታዊና ገንቢ ልምዶች የመጠበቅንና ይበልጥ የማጠናከርን አስፈላጊነት በማመን፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) እና (15) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•