በአገልግሎት ላይ

በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1314/2016)

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  መንግሥት በባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች ላይ የሚደረግ የአሠራር ውጤታማነታቸውንና የፋይናንስ አቋማቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን እርምጃዎች መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች ከግል ድርጅቶች ጋር በግልፅ ውድድር መሥራት የሚችሉበትን አቅም ለማጠናከርና ምርታማነታቸውንና ትርፋማነታቸውን ለመጨመር ለንግድ ቅልጥፍና ያላቸውን አመለካከት የሚቀይር አመቺ የሆነ የቁጥጥር ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት ባለቤትት የተያዙ የልማት ድርጅቶች አሠራራቸውን ለማሻሻል የሚያግዝ የቁጥጥርና አጠቃላይ የክትትል ሥርዓቶችን በመዘርጋት የመንግሥትን የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን ማጠናከር እና በእነርሱም ላይ የሚደረገውን አጠቃላይ ቁጥጥር ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች ተጠያቂነታቸውን በማረጋገጥና ግልፅነትን በማዳበር ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬት አስተዳደራቸውን ከዓለም ዐቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር ማጣጣሙ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ፤

በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች የሕዝብ አገልግሎት ግዴታቸውን በሚወጡበት ጊዜ ተገቢ ያልሆነ የአሠራርና የፋይናንስ ጫና ሳይኖርባቸው ሥራቸውን ማከናወን የሚያስችላቸውን ግልፅ ዓላማና የፋይናንስ ስርዓት ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶችን የፋይናንስ አፈፃፀማቸውን ማሻሻል እና የፊስካል ስጋትንና በመንግሥት ፋይናንስ ላይ የሚያሳድሩትን ጫና መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የልማት ድርጅቶች የሚሠሩበትን የሕግ ማዕቀፍን ማዋሃድና ማሻሻል ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ብሔራዊ ሀብት አስተዋጽዎ ለማድረግ የሚኖራቸውን አቅም የሚፈጠር መሆኑ ግንዛቤ በመወሰዱ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራሊዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1314/2016
ቀን: ግንቦት 8፥ 2016 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች