በአገልግሎት ላይ

የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ

ተቋማት ሲደራጁ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችል መልኩ ግልጽ ዓላማ ያላቸው፣ ከሌሎች ተቋማት ሥልጣንና ተግባር ጋር የማይጋጭና ተናባቢ የሆነ ተግባርና ኃላፊነት እንዲኖራቸው በማድረግ፣ በቅንጅት የሚሰሩ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ የሆነ፣ ብክነትን የሚቀንስና ውጤታማነትን የሚያበረታታ፣ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በየጊዜው የሚወጡ ሕጎች ወጥ የሆነ የተቋማት አደረጃጀትና ስያሜ ለመፍጠር ያልቻሉ በመሆኑ የተቋማት ቀጣይነትን ለማረጋገጥና የስያሜ ወጥነትን ለማስቀጠል ያልተቻለ በመሆኑ፣

በሥራ ላይ ያለውን የተቋማትን አደረጃጀትና ስያሜ ችግሮች በዝርዝር በጥናት በመለየት በየጊዜው የማይለዋወጥ፣ ዘላቂነት ያለው እንዲሁም ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ጋር አብረው እየተለወጡ የሚሄዱ የተቋማት አደረጃጀትና ስያሜን መፍጠር የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግሥት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣንና ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለው አወቀቃቀር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ  ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

 

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1263/2014
ቀን: ጥር 17፥ 2014 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1353/2016

ጥር 2፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1333/2016

ጷጉሜ 4፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1314/2016

ግንቦት 8፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1307/2016

ጥር 7፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1284/2015

ሚያዚያ 9፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 11/2013

ሐምሌ 2፥ 2013 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1233/2013

ግንቦት 12÷ 2013 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1236/2013

የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1205/2020

ሰኔ 23፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1183/2012

መጋቢት 29፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1176/2012

መጋቢት 16፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1146/2011

ነሐሴ 9፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ