በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ፣ ሌሎች መብቶችን የመጠቀም እድሎችን ለማስፋት፣ የአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት ላይ እምነት እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የግልጽነት፣ የተጠያቂነት እና የተሳለጠ አሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል በመሆኑ፤
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ፣ መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት፤ ሀገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ በመሆኑ፤
የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ በመዘርጋት፣ አስተማማኝ፣ ተደራሽ እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ሥርዓትን ማጎልበት፣ የሀገሪቱን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ተገማችነትን ለማሳደግ፤ የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የሚረዳ በመሆኑ፤
ሁሉን አቀፍ፣ ወጥና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ የሀገሪቱ ነዋሪዎች የሚመዘገቡበትን ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በመዘርጋት እና የተመዝጋቢዎችን መረጃ በመያዝ የዲጂታል መታወቂያ አጠቃቀም ሥርዓትን ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ፤ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አካላት ማለትም ተመዝጋቢ፣ መዝጋቢ፣ ተጠቃሚ አካላት፣ አረጋጋጭ አካላት እና በዲጂታል መታወቂያ ተቋም መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በሕግ የሚመራበትን የመተማመኛ ማዕቀፍ መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•