የመንግሥት ሠራተኞች የሰው ኃይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ እንዲመሠረት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት፣ ተግባርና ተልዕኮ በብቃት፤
በጥራትና በውጤታማነት እንዲወጡ ለማድረግ፣ ዘመናዊ የሆኑ የአሠራር ሥርዓት በመከተል፣ ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ኢትዮጵያን የሚመስል የመንግሥት ሠራተኞች ስብጥር ማለትም ብዝኃነት እና አካታችነትን ያገናዘበ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት መገንባት ጠቃሚ በመሆኑ፤
የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓትን መዘርጋት፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሥራን ለማሻሻል፣ ምርታማነት ለመጨመርና ለማጎልበት፣ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማግኘት እና በሥራ ላይ ያሉትንም ለማቆየት ወሳኝሆኖ በመገኘቱ፤
የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርና አደረጃጀት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ፤ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎትና ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል፤
የመንግሥትን የመፈፀም ብቃት በማጎልበት፣ የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካ እና ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ሊያሸጋግር የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤ በሠራተኞች መካከል ጤናማ ተወዳዳሪነት ለመፍጠር የሚያስችል የማትጊያ እና የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•