በሥራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 በይዘት እና አፈፃፀም ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ፤
የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅን የተፈፃሚነት ወሰን በማስፋት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የመንግሥት ግዥ አፈፃፀምና ንብረት አስተዳደር ሥርዓቱን ግልፀኝነት በማሻሻል እና ተደራሽነቱን በማስፋት በመንግሥት ግዥ አፈፃፀምና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ የሚከሰት የሕግ ጥሰት የሚያስከትለውን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ግልፅ ማድረግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ-አንቀጽ 1 መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡