የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የአስተዳደር በደል ለመከላከል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ምርመራ በማካሄድ በደሎች እንዲታረሙ የማድረግ አቅሙን ማሳደግ በማስፈለጉ፤
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን አቋም ማሻሻል፣ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና የማዕከላት አደረጃጀት፡ የሠራተኞች አስተዳደር እና የተቋሙን ነፃነት ማረጋገጥ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣
አሁን ሀገሪቱ ከደረሰችበት እድገት አንጻር የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በማስፋት በግል ድርጅቶች የሚፈጸሙ የአስተዳደር በደሎችን አቤቱታ መቀበል እና ምርመራ ማካሄድ በማስፈጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011ን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (15) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•