በአገልግሎት ላይ

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ

የሽብር ድርጊት በሰው ልጆችና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ ወንጀል ሲሆን፤ ለአገራችንና ለዓለም ህዝብ ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት መሆኑን በመገንዘብ፤

መንግስት የአገርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ወንጀሉን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባህሪውን ያማከለ ጠንካራ ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት ማድረግ እንዲሁም አጥፊዎች ከድርጊታቸው ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፤

ኢትዮጵያ የሽብር ድርጊትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የፀረ-ሽብር ዓላማ ካላቸው አገራት ጋር ለመተባበር እና አባል የሆነችባቸውንና የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በተለይ በተባበሩት መንግስታትና በአፍሪካ ህብረት የተደረጉት ስምምነቶችንና የተላለፉ ውሳኔዎችን ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊነቱ የታመነበት በመሆኑ፤

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ወጥቶ የነበረው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 በይዘትና አፈጻጸም ክፍተቶች የነበሩበት በመሆኑ በዜጎች መብት እና ነጻነት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ያሳደረ ሆኖ በመገኘቱ፤ የግለሰቦችን መብቶችና ነፃነቶች በበቂ ሁኔታ ሊያስጠብቅና የህግ አሰፈጻሚ አካላትን ተጠያቂነት ማስፈን በሚያስችል ሕግ መተካት በማስፈለጉ፤

የሽብር ድርጊት ተጎጂዎች የህክምና፣ መልሶ ማቋቋምና መሰል ተግባራት ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት መፍጠር በማስፈለጉ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (5) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1176/2012
ቀን: መጋቢት 16፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found