የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የሀገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት የሚገታ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ የህግ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በሀገራችን የተጀመረውን የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል ስነ-ምግባር የተገነባ፣
ለኮሚሽኑ በተለያዩ አዋጆች የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በአንድ ላይ ማሰባስብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና ኮሚሽኑ በሀገር ደረጃ የፀረ ሙስና ትግሉን የመምራት እና የማስተባበር ሚናውን ለመወጣት የሚያስፈልገውን የኃላፊነት ወሰን በህግ መደንገግ በማስፈለጉ፤
የሙስና መከላከል ተግባር በአንድ ተቋም ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ኮሚሽኑ ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚኖረው ግንኙነት የህግ ድጋፍ እንዲኖረው በማድረግከፀረ ሙስና ትግል አኳያ በአለም አቀፍ እና በአህጉር ደረጃ ሀገሪቱን በብቃት እንዲወከል ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
•
•
•
•
•
•
•
•
•