በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሩሲያ ፌደሬሽን መንግሥት መካከል የተደረገው የንግድ ስምምነት ኅዳር 17 ቀን 1992 ዓም በሞስኮ የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ በሚገባ በሥራ ላይ የሚውለው፡ በተዋዋይ አገሮች ሕጎች መሠረት ስምምነቱ መፅደቁን ተዋዋይ ወገኖች በዲፕሎማቲክ አካላት አማካይነት አንዱ ለሌላው ካሳወቁበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተገለጸ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 1992 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•