የኢኮኖሚ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር የሚገኝ ስራ ክፍል ሲሆን በዋነኛነት ከታክስ እና ግብር ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን፣ የጉምሩክ ወንጀሎችን እንዲሁም እንደ አእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰት፣ የሸማቾች መብት ጥሰት፣ አራጣ፣ የውጪ ምንዛሬ በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ መገኘት፣ ሃሰተኛ ገንዘብ ማዘጋጀት እና ስርጭት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን እና መሰል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ልዩ ልዩ ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎችን ምርመራ በመምራት፣ በፈጻሚዎች ላይ ተገቢውን የወንጀል ክስ በማቅረብ እና የሕዝብን እና የመንግሥትን ጥቅም አስጠብቆ በመከራከር አጥፊዎች በሕግ የተቀመጠውን አስተማሪ ቅጣት እንዲቀጡ የሚሰራ ሲሆን፤ በክልል ደረጃም በአዳማ፣ ኮምቦልቻ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር እና ጅግጅጋ ቅርንጫፎች አማካኝነት ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች ላይ ምርመራ እና የወንጀል ክስ ክርክር በማድረግ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የስራ ክፍል ነው፡፡