ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው 189 ስማርት ሞባይሎችን ይዞ የተገኘው ተከሳሽ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

Accused Found with Over 1 Million Birr in Undeclared Smartphones Sentenced to Imprisonment and Fine

እንግዳው ማሞ የተባለው ተከሳሽ ዕቃው ተገቢውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመበት መሆኑን እያወቀ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡30 ሰዓት ላይ በሱማሊ ክልል በፋፈን ዞን በቦንባስ ከተማ አካባቢ ባለው የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ ለመንግሥት ሊከፈል የሚገባውን 1 ሚሊዮን 263 ሺ 424 ብር የሆነ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈል ግምታዊ ዋጋቸው 4 ሚሊዮን 8 ሺ ብር የሆኑ በውጭ ሀገር የተመረቱ የተለያየ ሞዴል ያላቸው በቁጥር 189 ስማርት ሞባይሎችን ተከሳሽ በሚያሽከረክረው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3-A59269 አ/አ በሆነ መኪና ላይ በተበጀው ሻግ ውስጥ ጭኖ ከጂግጂጋ ወደ ሀረር አቅጣጫ እያጓጓዘ እያለ የተያዘ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በጅግጅጋ ማስተባበሪያው መሠረት የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 168/2/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በሱማሊ ክልል ፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት በፈፀመው የኮንትሮባንድ ዕቃ ማጓጓዝ ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ መሠረት የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ50 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡

Tagged Under: CourtVerdict • CriminalSentencing • Smuggling
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች