ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ የንግድ ትርፍ ግብርን አሳውቃ ያልከፈለችው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣች

Individual Sentenced to Imprisonment and Fine for Failing to Pay Over 25 Million Birr in Business Income Tax After Declaration

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ 25 ሚሊዮን 385 ሺ 666 ብር የንግድ ትርፍ ፍሬ ግብርን አሳውቃ ባልከፈለችው ግለሰብ ላይ ክስ አቅርቦባት በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ40 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ አድርጓል፡፡

እመቤት መላኩ የተባለችው ተከሳሽ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 116/2/ እና 125/1/ን በመተላለፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 01 በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝግባ የንግድ ስራ ስትሰራ የቆዬች ሲሆን በግብር ስወራ ወንጀል ከ2004 እስከ 2010 በተደረገው የኢንቨስትጌሽን ኦዲት ግብር ለመሰወር በማሰብ ግዥ ያልተፈጸመባቸው 72 ሀሰተኛ ደረሰኞችን ግዢ እንደተፈፀመባቸው በማስመሰል በሂሳብ መዝገብ ውስጥ በማካተት ለግብር ሰብሳቢው ተቋም በማሳወቅ የሚፈለግባትን አጠቃላይ የንግድ ትርፍ ግብር ፍሬ ግብር 25 ሚሊዮን 385 ሺ 666 ብር አሳውቃ ባለመክፈሏ በፈጸመችው የንግድ ትርፍ ግብር ስወራ ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባታል፡፡

ተከሳሿ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የተከሰሰችበት ክስ በችሎት ተነቦላት የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ያለች ሲሆን ዐቃቤ ሕግም 2 የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ በበቂ ሁኔታ ያስረዳ በመሆኑ ተከሳሿ በቀረበባት ክስ መሠረት እንድትከላከል ብይን ሰጥቷል። በሰጠው ቀጠሮ መሠረት 1 የመከላከያ ምስክር አቅርባ ብታሰማም የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችንና ማስረጃዎችን ማስተባበል ባለመቻሏ ትከላከል በተባለችበት ድንጋጌ ስር የጥፋተኛ ፍርድ በመስጠት በ2 ዓመት ጽኑ እስራትና በ40 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: ababa • addis • addis ababa • Auditing • business • conviction • court • Crime • Economic • Economic Crime • evasion • federal • Federal High Court • fine • Fraud • high • imprisonment • Income • Income Tax • legal • legal case • Tax • tax administration • Tax Evasion • Tax Fraud • tax law violation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች