በሕገ-ወጥ መንገድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ጥፍጥፍ ወርቅ ይዞ ሲያዘዋውር የተያዘው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

Individual Caught Trafficking Over 3 Million Birr Worth of Unprocessed Gold Illegally Charged

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ አማረ ዮሃንስ በተባለው ተከሳሽ ላይ የወንጀል የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በ1ኛ ክሱ ላይ ተከሳሽ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በኃላፊነቱ ወይም በሥራ ግዴታዉ ማድረግ የሚገባዉን እንዳያደርግ በማሰብ የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡40 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ የሀገር ዉስጥ በረራ በሚባለዉ ቦታ ተከሳሽ በብርበራ ከለበሰዉ ጃኬት ዉስጥ የተያዘዉን ሶስት የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉ የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ ሲያዘዋውር በፖሊስ አባላት ሲያዝበት በቦታዉ የነበረዉ የሻምበል አዛዥ የሆነዉን የዐቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑትን ንግድ ፍቃድም የለኝም፤ ነጋዴም አይደለሁም የተያዘዉን ወርቅ ግማሹን ልስጥክ እና ልቀቀኝ በማለት የተያዘዉን ወርቅ ብዛት ግማሽ በጉቦ ያቀረበ በመሆኑ በፈጸመው ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

በተመሳሳይ በ2ኛ ክሱ ተከሳሽ ከላይ በ1ኛ ክስ ዉስጥ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በቦታዉ በመደበኛ ስራቸዉ ላይ የነበሩት የፖሊስ አባላት ተከሳሽን አካላዊ ፍተሻ ሲፈትሹ ምንም አይነት የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ በለበሰው ጃኬት ዉስጥ ሶስት ጥፍጥፍ ወርቅ የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉን የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን ወርቅ የከበረ ማዕድን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ በፍተሻ የተገኘ በመሆኑ የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ ማዕድን በተፈጥሮአዊ ሁኔታዉ መያዝ ወንጀል ተከሷል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን ተከሳሽ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት መቃወሚያ የለኝም በማለት ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ ለማሰማት ለመጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Tagged Under: Amhara • bole international airport • bribery • charges • Contraband • Corruption • court • court hearing • criminal • Criminal Charges • Customs violation • district • federal • gold • gold smuggling • high • illegal • judicial process • lideta • lideta district court • mineral resources • police officers • Smuggling • trafficking • unprocessed gold
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች