ሀና ግዛው ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በኢፌዲሪ የፍትሕ ሚኒስቴር በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በተደራጁ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል፣ በሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል እና በንብረት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ስር በዐቃቤ ሕግነት እንዲሁም በሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ስር በቡድን አስተባባሪነት አገልግለዋል። ከዚያ በመቀጠልም የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል በምክትል ዳይሬክተር ጀነራልነት ያገለገሉ ሲሆን በዚያ ጊዜ ውስጥ ከሰሯቸው ዋና ዋና ስራዎች ውስጥ በብሔራዊ ፀረ-ሙስና ኮሚቴ ሥር የሚሰሩ ሥራዎች ለማከናወን የተመደቡ ልዩ የምርመራና የዐቃቤ ሕግ ቡድኖችን የማስተባበር ስራ አንዱ ነው። በአሁኑ ወቅት የኢኮኖሚ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዳይሬክተር ጀነራል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በሕግ ዘርፍ ያካበቱት ከ12 ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ ለሥራቸው ተገቢው ዕውቀትና ልምድ እንዲኖራቸው አድርጓል።