በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር የሚገኝ ስራ ክፍል ሲሆን በፌደራል መንግሥቱና ለፌዴራል መንግሥቱ ተጠሪ በሆኑ ከተማ አስተዳደሮች ተቋማት ውስጥ የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን ምርመራ የመምራት፣ ውሳኔ የመስጠትና በፍርድ ቤት ተከራክሮ ማስወሰን ኃላፊነት ያለበት የሥራ ክፍል ነው፡፡ የሥራ ከፍሉ የሙስና ወንጀል ምርመራን መምራትና ምርመራዎች በሕግ አግባብ እየተሰሩ መሆናቸውን መቆጣጠር፣ የሙስና ወንጀል ክስ ማቅረብና መከራከር እንዲሁም ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ሕጋዊ አስተያየቶችን የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡ የሥራ ክፍሉ በተለይ ከባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ በማተኮር በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ላይ የተመለከቱ የሙስና ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ ተገቢውን የሕግ ማስከበር ስራ በመሥራትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ሙስና አትራፊ አለመሆኑን ማረጋገጥ ዋነኛ ኃላፊነቱ ነው፡፡
