ዘላለም ፈቃዱ

ዳይሬክተር ጀነራል
መስከረም 1፣ 2009 ዓ.ም. – አሁን

ዘላለም ፈቃዱ ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክተር ጀኔራል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። በኃላፊነት ቆይታቸው በስራ ክፍሉ ብልሹ አሰራሮችን በመዋጋት እና የሙስና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ በማቅረብ በሀገር ደረጃ ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ረገድ ተፅዕኖ ያላቸው አመርቂ ስራዎችን ተሰርተዋል። ከ15 ዓመታት በላይ በዘለቀ የፀረ-ሙስና ሕግ ማስከበር ተሳትፎ ዘላለም የሙስና ወንጀልን በመመርመር እና በመክሰስ ረገድ ሰፊ ልምድ አካብተዋል። ዘላለም አሁን ከያዙት ኃላፊነት በፊት የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል፣ የሙስና እና ንብረት ማስመለስ ማስተባበሪያ አስተባባሪ፥ የፀረ-ሙስና ዐቃቤ ሕግ እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል።

ዘላለም የታማኝነት፣ የተጠያቂነት እና የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በኢትዮጵያ እንዲሰፍኑ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ይሰራሉ። አሁን ካለው ኃላፊነት በተጨማሪም ዘላለም የፀረ–ሙስና ትግል ለማጠናከርና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመስራት በከፍተኛ ሁኔታ ይጥራሉ። በፀረ-ሙስና ትግል ላይ የተሰማሩ አካላትን አቅም ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎችም በቁርጠኝነት አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡

የትምህርት ዳራ

  • የመጀመሪያ ዲግሪ በህግ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
  • ሁለተኛ ዲግሪ በንግድ ህግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ