የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ345 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ግዥ በመፈፀም እና 10 ሚሊዮን ብር ጥቅም በመቀበል በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን የቀድሞ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ያለመከሰስ መብት አነሳ

House of Peoples' Representatives Lifts Immunity of Former Bule Hora University President Suspected of Over 345 Million Birr Illegal Procurement and Receiving 10 Million Birr in Bribes

የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ ከ345 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ግዥ በመፈፀም እና 10 ሚሊዮን ብር ጥቅም በመቀበል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ያለመከሰስ መብቱ መነሳቱን በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት አቶ ዘላለም ፈቃዱ ገለፁ፡፡

ምክትል ጄኔራሉ በዩኒቨርስቲው በተደረገው ምርመራ ዋጋቸው 116 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ከዩኒቨርስቲው የካፒታል በጀት ቀንሰው ለተለያዩ ተቋራጮች 14 ተሽከርካሪዎችን እና ማሽነሪዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ተገዝቶ ሰጥቷል፤ በወቅቱ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ BHU Consulting Engineers General Level 1 PLC የተባለ ድርጅት አቋቁመው የዚሁ ድርጅት ስራ አስኪያጅ በመሆን ለዚሁ ድርጅት ከዩኒቨርስቲው ሀብት ላይ 23 ሚሊዮን 478 ሺ 150 ብር እንዲከፈል በማድረግ ከዚህ ገንዘብ ላይ 2 ሚሊዮን 116 ሺ 16 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግል አካውንታቸው ላይ ገቢ እንዲሆን አድርገዋል ብለዋል፡፡

ምክትል ጄኔራሉም ከመንግሥት የግዢ ሕግና መመሪያ ውጭ ያለምንም ጨረታና ውድድር በቀጥታ እንዲፈፀም በማድረግ ለ9 የተለያዩ ተቋራጮች 195 ሚሊዮን 52 ሺ 812 ብር የሚያወጣ የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን ሰጥተዋል፡፡ ከዩኒቨርስቲው ጋር ቀጥተኛ የስራ ግንኙነት ካላቸው 3 ድርጅቶችና ግለሰቦች በባለቤታቸው ስም 10 ሚሊዮን ብር ተቀብለዋል፡፡ በዚሁ ብር በባለቤታቸው ስም 72 ካሬ ላይ ያረፈ ባለሶስት ወለል ህንፃ ገዝተዋል በሚል እንደተጠረጠሩ አቶ ዘላለም ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተነሳው የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ ላይ በህገ-ወጥ መንገድ ሀብት ማፍራት እና በሌሎች በተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች በሥልጣን አለአግባብ መገልገል፣ ጉቦና የማይገባ ጥቅም መቀበል፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራትና ህገ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡

እኛም ጉዳዩን ተከታትለን መረጃዎችን የምናደርሳችሁ መሆኑን እንገልጻልን

Tagged Under: asset forfeiture • bribery • bule • bule hora university • capital budget • conflict of interest • contract award • Corruption • dr. • dr. chala wata • embezzlement • ethiopian federal democratic republic • federal attorney general • Financial Crime • hora • house • house of peoples’ representatives • illegal • illegal procurement • illicit enrichment • immunity • Investigation • misuse of public funds • parliamentary • parliamentary immunity • peoples' • Representatives • university
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች