የትግራይ ክልል ፍትህ አካላት አቅም ማጎልበት ላይ ያለመ ስልጠና ተሰጠ

Training Provided to Tigray Region Justice Bodies on Capacity Building

ለትግራይ ክልል ፍትሕ አካላት (ዳኞች፣ ዐቃቤያነ ሕግ እና መርማሪ ፖሊሶች) በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ምርመራ እና ክስ አሠራር ስርዓት ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ከሲቪፖል (CIVIPOL) ጋር በመተባበር የሶስት ቀናት ሥልጠና በቢሾፍቱ ከተማ ተሰጥቷል።

በሥልጠናው መርሀ-ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እንደገለፁት የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማ የትግራይ ክልል ፍትሕ አካላት በሰዎች መነገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን አስከፊነት በመረዳት የፍትሕ አካላት ተገቢውን ምርመራ፣ ክስ እና ችሎት ክርክር ሂደት ወይም ፍርድ ሂደቱ ላይ ተገቢውን እውቀት እና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል እንደሆነ ገልፀዋል። አያይዘውም በፍትሕ አካላት መካከል የሚኖረውንም ቅንጅታዊ አሠራር ለማጠናከር እንደሚረዳ አመላክተዋል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ በሰዎች የመነገድ እና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ የማሻገር ወንጀሎችን ለመመርመር እና ለማስቀጣት የተዘጋጀ የአሠራር ስርዓት ላይ ሲሆን የወንጀሎቹ ምንነት በዓለም ዓቀፍ ሕግ እና በሀገር ውስጥ ህጎች፣ ወንጀሎቹን መመርመርና ማስቀጣት፣ የወንጀል ተጎጂዎች ጥበቃ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መሠረት ያደረገ ነበር።

ይህ ሥልጠና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ከብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት እና ሲቪፖል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ሥልጠናውም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል።

Tagged Under: bishoftu building capacity Capacity Building civipol Criminal Investigation Criminal Prosecution Education ermias yemaneberhan human Human Trafficking International law judicial judicial officers Justice Justice System learning Legal Training Prosecutors region skill development Smuggling system Tigray tigray region trafficking Training Victim protection
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች