የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

The Ministry of Justice of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the Addis Ababa Police Commission have signed a cooperation framework agreement

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችል በወንጀል ምርመራ፣ ክስ እና ክርክር ሂደት ላይ በጋራ የሚተገበሩ ጉዳዮችን በተሻለ ቅንጅት እና ውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

በትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርአያሥላሴ በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚደረገው የጋራ ስምምነት በወንጀል ምርመራ እና ክስ ሂደት ላይ የሚኖረውን የተልዕኮ አፈጻጸም ከማቀላጠፍ ባለፈ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ላይ መሠረታዊ የሥራ ባህል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣዩ ዓመት በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የተሻለ ውጤትን ለማምጣት ከወዲሁ በቅንጅት የመሥራት ሂደቱን በመጀመር የሥራ አፈፃፀሙንም እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት ለአንድ ዓላማ የሚተጉ ተቋማት በመሆናቸው እንዲሁም ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው የፍትሕ ጥያቄዎች በተናጠል ምላሽ መስጠት ስለማይቻል ተቀናጅቶ በጋራ መስራቱ አገልግሎቱን የተሟላ የሚያደርገው መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ስምምነት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከአንዱ ወደ ሌላኛው አካል እየተመላለሱ የቆዩ የወንጀል መዛግብትን አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል እንዲሁም በቀጣይ የሚኖረውን አጠቃላይ የወንጀል ፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Tagged Under: ababa addis addis ababa addis ababa justice bureau Addis Ababa Police addis ababa police commission Addis Ababa Science and Technology University agreement commission constitution of the federal democratic republic of ethiopia Cooperation democratic ethiopia federal democratic republic federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) federal democratic republic of ethiopia constitution framework Justice ministry mission operation per Police police commission public ratio republic work
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች