በፍልሰት ዙሪያ የሚሰሩ ብሔራዊ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ፎረም የመጀመሪያ ዙር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

The National Civil Society Organizations Forum on Migration is holding its first round of dialogue platform

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በብሔራዊ ትብብር ጥምረት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በፍልሰት ዙሪያ የሚሰሩ ብሔራዊ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ፎረም የመጀመሪያ ዙር የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

በመድረኩ መንግሥት ፍልሰት የልማትና የማህበረሰብ ዕድገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በማመን  ፍልሰትን መደበኛና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚኝ ተመላክቷል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 መሰረት በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን በመከላከልና በመቆጣጠር በአጠቃላይም በፍልሰት አስተዳደሩ ውስጥ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል።

የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶቹ ሚናቸውን እንዲያጎለብቱና በተባበረ ክንድ አገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ሴክሬቴሪያት ከጂ.አይ.ዜድ በተገኘ ድጋፍ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አገር አቀፍ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ፎረም እንዲመሰረት ስምምነቶች መደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፤

ፎረሙም በመግቢያ ስምምነት ሰነዱ መሰረት የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ከመንግስት በኩል ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ከፎረሙ ተመራጭ አመራሮች እና ከሴቭ ዘ ቺልድረን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከምስረታው በኋላ የመጀመሪያውን የምክክር መድረክ ማዘጋጀቱና ለፎረሙም ህጋዊ ዕውቅና እንደሚሰጠውም ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ የሲቪክ ማሕበረሰብ ድርጅቶች የብሔራዊ የትብብር ጥምረት አባላት፣ የዓለም ዓቀፍና የኢንባሲ ተወካዮች እና የሲቪል ማሕበረሰብ ፎረም ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ውይይቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Tagged Under: 1178/2012 8/2012 african charter on the rights and welfare of the child agency for civil society organizations civil Civil Society civil society authority civil society law Civil Society Organizations civil society organizations (csos) civil society organizations authority civil society organizations proclamation no. 1113/2011 dialogue first Forum holding international organization for migration international organization for migration (iom) Migration National old organ organization organizations platform ratio society un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች