ሐና አርዓያሥላሴ ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
ወ/ሮ ሐና ከዚህ ኃላፊነታቸው አስቀድመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል እና ዋና ኮሚሽነር በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ከፍተኛ የፖሊሲ ጥናት ባለሙያ ሆነው ሰርተዋል።