በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዘርፍ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ

Nine-Month Performance Plan Review Conducted at the Dire Dawa Branch Office of the Attorney General Sector, Ministry of Justice

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በተገኙበት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባን ጨምሮ አቶ በረከት ማሞ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ታደሰ እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ሁሉም ሠራተኞች በተገኙበት የጽህፈት ቤቱ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ተገምግሟል፡፡

የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቃሲም አማን የ2016 በጀት ዓመት የጽህፈት ቤቱን የዘጠኝ ወራትን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና ግቦች አፈጻጸም፣ በዕቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተለዩ ጥንካሬዎች እና ውስንነቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ በቀረበው ሪፖርት ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ሰራተኞችም በብዙ የስራ ጫና ውስጥ ሆነው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ በማስቻላቸው ምስጋናቸውን በማቅረብ የጽህፈት ቤቱ ስራ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ያለው አጽተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን በመግለጽ ቀሪ ስራዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ስራዎች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ግዜያት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠልም የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዐቃቤ ሕግ እና የፖሊስ ቅንጅታዊ ሥራ ያለበትን ደረጃ የገመገሙ ሲሆን በዚህም የምርመራ መዛግብት አፈፃፀም፣ የምስክሮችና ተከሳሾች አቀራረብ እና ተያይዥ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን አፈፃፀሙ እየተሻሻለ መምጣቱን እና በቀጣይ መስተካከል ያሉባቸውን ጉዳዮች በመለየት ትኩረት በመስጠት መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

Tagged Under: attorney Attorney General Budget budget year case management dawa dire Dire Dawa general government agency Implementation Judicial System legal sector nine-month office performance performance Performance Review plan plan implementation police cooperation progress progress report report review stakeholder stakeholder meeting witness testimony year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች