የፍትሕ ሚኒስቴር 16ኛዉን ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል አከበረ

Ministry of Justice Celebrates the 16th National Flag Day

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሶትቱም ዘርፎች ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የስራ ኃላፊዎች እና የተቋሙ ሰራተኞች እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ አባላት በተገኙበት አከበረ፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጉዲዮን ጢሞቲዎስ የዘንድሮዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር የአንድነታችን ምልክት የሆነዉ ሰንደቅ ዓላማችን ምልክታችን ሆኖ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከአገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ የሚዉለበለብበት ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ከበአሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን መልእክቶች አስተላልፈዋል፡፡

ቀጥሎም የተዘጋጀዉ ሰንደቅ ዓላማው በፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል ህጎች ተፈፃሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ አማካኝነት ተሰቅሏል፡፡

ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነዉ” በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

Tagged Under: celebration communication day democratic dr. dr. gideon timotheos FDRE federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) Flag gideon National National Flag Day national symbol National Unity patriotism public relations republic sovereignty timotheos
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች