''መንግስት ባለፉት ዓመታት በሲቪል ማህበራት ዘርፍ ባከናዎናቸው የሪፎርም ተግባራት ሲቪክ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሰፋቱ ተገለፀ''

"The Civic Space has Expanded More than Ever Due to the Reform Activities Carried Out by the Government in the Civil Society Sector Over the Past Years."

ለሶስት ቀናት የሚቆየዉ 5ኛዉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ማስጀመሪያ መድረክ በአዲስ አለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።

በስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት: የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመከበሩ በተጨማሪ ተቋማቱ በሃገር ግንባታ ሂደት ዉስጥ ያላቸውን የማይተካ ሚና በማጠናከር አጋርነታቸውን የሚያረጋግጡበት ነዉ።

አቶ አደም አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በመንግስት ለተያዘዉ ሀገራዊ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራ ስትራቴጂያዊ አጋር በመሆን የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ በማረጋገጥ ገንቢ ሚና ከመጫወታቸዉ በተጨማሪ መንግስት በሚከተለዉ የብዘሃ-ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫ እንደ አንድ ተዋናይ በመንቀሳቀስና የዘርፉን ክፍተቶች በመሙላት ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ተቋማቱ በትዉልድ መካከል እና በማህበረሰብ ዘንድ ሊኖር የሚገባውን ትስስር በማጠናከር ረገድ የሚጫወቱት ሚና የላቀ መሆኑን በማስታወስ ሃገራዊ ለዉጡን ተከትሎ በመንግሥት የተተገበሩ የህግ እና አሰራር ሪፎርሞችም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱበትን ምህዳር በማስፋት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር እንዳስቻለም አስረድተዋል።

በሃገራችን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ታሪክ አሁን የምንገኝበት ወቅት “ወርቃማው ዘመን” ተብሎ ሊገለፅ የሚችል እንደሆነና ተቋማቱ እርስ በርስም ሆነ ከመንግሥት ጋር ያላቸውን ትስስር በእጅጉ በማሻሻል አዎንታዊ ሚና መጫወት የሚችሉበትን እድል ማስፋት ያስቻሉ ስራዎች መተግበራቸዉንም በማስታወስ የተመቻቸውን እድል በመጠቀም አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላደረጉ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።

የለዉጡ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አፅንኦት ሰጥተዉ: ሃገራዊ መግባባትንና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታን በማገዝ: ህዝባችንን ከተረጂነት ለማዉጣት የሚደረገውን ትግል በመደገፍና ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎቻቸዉን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች አንፃር በመቃኘት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሃገራችን በኢፍትሃዊ አካሄድ ያጣችዉን የባህር በር የማግኘት ጥያቄ በአለማቀፍ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን እና የአብዛኞቹን ሃገራት ድጋፍ እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የኢትዮጵያን መንግስትና ህዝብ በመወከል ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም ድርጅቶቹ በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የሚጠበቅባቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲወጡ በአደራ ጭምር አሳስበዋል።

ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉ በስኬት የሚነሱ መኾናቸውን አስረድተዋል።

ምንጭ፡- የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

Relevant Departments and People
Tagged Under: act activities african charter on the rights and welfare of the child agency for civil society organizations and healthcare administration and control authority arra (agency for refugees and returnees affairs) banking sector reform car civic civil civil and political rights civil service reform Civil Society decree due Government government law and justice services sector judicial law legal legislation Policy proclamation reform Regulation sector society space statute year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች