በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን ከተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ መንግስቴ ጋር በጋራ በመሆን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳትና ግንባታ ስራ ያለበትን የስራ ሁኔታ ጎብኝተዋል።
የህንፃ ዕድሳትና የግንባታ ስራው በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተሰራ የሚገኘው የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ህንፃ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ተግዳሮቶችም እንደገጠሙት በስራ ተቋራጩና በአማካሪ ድርጅቱ ለክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በጉብኝቱም ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የህንፃ ዕድሳትና የግንባታ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑንና ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ ያለውን የስራ አንቅስቃሴ አድንቀው እንደ ችግር የተነሱ ነጥቦችን በተቋሙ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ እንደሚሰጥ በመግለፅ ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡