የተሻለ የፍልሰት አሥተዳደር ሥርዓትን ለመዘርጋት በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

It was pointed out that it is necessary to work in coordination to establish a better migration management system

ትኩረቱን በብሔራዊና ክልልላዊ ትብብር ጥምረቶች የ2017 ዓመታዊ ቅንጅታዊ የሥራ እንቅሰቃሴ እና የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት መስኮች ላይ ያደረገ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የትብብር ጥምረቱ እንዲሁም የክልሎች የተጠቃለለ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በዚህም ወቅት በፍልሰት አስተዳደር ዙሪያ ትላልቅ የሚባሉ ተግባራት እንደተከናወኑ እና በዋናነትም የብሔራዊና የክልል የትብብር ጥምረት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ የብሔራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በተገኙበት ሰኔ 28/2017 ዓ.ም መፅደቁ ተገልፆል።

በተጨማሪም በሰዉ መነገድና ሰዉን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር እንዲኖር ለማስቻል ዓለም ዓቀፍ ህጎችን ከማፅደቅ ጀምሮ አገራዊ የሕግ ማዕቀፎችን በማዉጣት የትብብርና የቅንጅት አደረጃጀቶች ተዘርግተዉ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በጥምረቱ አደረጃጀቶች ላይም ማሻሻያ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት በብሔራዊና በክልል ትብብር ጥምረቱ በግንዛቤ መፍጠር፤ የተጎጅዎች ድጋፍና መልሶ ማቋቋም፤ በዉጭ አገር የስራ ስምሪት፤ በሕግ ማስከበር ፤ በዲያስፖራ ተሳትፎና ልማት፤ በፍልሰት መረጃ አስተዳደር፤ በፍልሰት ምርምር የስራ ቡድኖች በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

ማሕበረሰቡ ጋር የሚሰሩ ስራዎች ትርጉም ያላቸዉና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ የሚሄዱ መሆን እንዳለባቸዉ እና ለዚህም በተግዳሮትነት የሚነሱ ነገሮችን በመለየት ተመጣጣኝ መፍትሄ እያስቀመጡ ለዉጤቱ መትጋት እንደሚገባ የተመላከተ ሲሆን በተያያዘም የአገር ዉስጥ ህገ ወጥ የህፃናት ዝዉዉር ጉዳይ ተያይዞ ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ሉሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የውይይት መድረክ በነገው መርሃ-ግብርም የትብብር ጥምረቶቹ የ2018 ዓ.ም የትኩረት መስኮች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ እና አቅጣጫ እንደሚሰጥባቸው ይጠበቃል፡፡ መድረኩን የፍትሕ ሚኒስቴር ከአለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) እንዲሁም ከአለማቀፉ የፃናት አድን ድርጅት ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል፡፡

Tagged Under: 2017 agreement 2017 budget 2017 budget year 2017 proclamation 2017 ratification age better case management system Coordination data management system information management system international organization for migration (iom) iom lis management management information system (mis) Migration Migration Management national migration cooperation coordination office national migration coordination secretariat national migration coordination unit point point of sale system ratio records management system system work
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች