የሕግና ፍትሕ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በላይሁን ይርጋ ክፍሌ

ሚኒስትር ዴኤታ

በላይሁን ይርጋ ክፍሌ በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ህግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ከህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በዚህ ኃላፊነት ማገልገል ከመጀመራቸው አስቀድሞ ከነሐሴ 01 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከፍተኛ የፖሊሲና የህግ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዳይሬክተር ጄኔራል፣ ቡድን አስተባባሪ እና ዐቃቤ ህግ እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግና ጀማሪ ዐቃቤ ህግ በመሆን ከ ህዳር 01 ቀን 2002 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በፍትህ ሚኒስቴር አገልግለዋል።

ከ15 ዓመት በላይ ባካበቱት ልምድ በላይሁን ይርጋ በኢትዮጵያ የሕግ የበላነት እንዲረጋገጥ እና ፍትሕ እንዲሰፍን በቁርጠኝነት ለማገልገል ዝግጁ ናቸው።

የትምህርት ዳራ

  • መቀሌ ዩኒቨርስቲ፣ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ
  • አምስተርዳም ዩንቨርሲቲ ከመቐለ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ የህግ ረቂቅ ጥናትና ማርቀቅ ሁለተኛ ዲግሪ

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

News From State Minister for Legal and Justice Service Division