የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ

Attorney General Sector Branch Offices Monitoring Directorate Reviews its 2016 Budget Year Performance Report

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን አቅርቦ ግምገማ አካሄደ፡፡ በሪፖርቱም በስሩ ካሉት አስራ ሶስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌቱ ታደሰ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ምርመራቸው ተጠናቀው በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መወሰን ካለባቸው 49,231 የወንጀል የምርመራ መዝገቦች ውስጥ 48,570 (98.7%) መዝገቦች ላይ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በዐቃቤ ሕግ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው ላይ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በሁሉም የወንጀል ክርክር መዛግብት የመርታት ምጣኔን እንዳብራሩት ከሆነ በተከሳሽ 92%፣ በመዝገብ 95% ለማድረስ ታቅዶ በክርክር ላይ ከነበሩ 34,961 መዛግብት እና 42,081 ተከሳሾች ውስጥ ፍርድ ቤት በ12,297 መዛግብት እና በ15,233 ተከሳሾች ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል፤ በ11,960 መዛግብት እና በ14,781 ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት፣ በ337 መዛግብት እና በ452 ተከሳሾች ላይ ነፃ በማለት ፍርድ ሰጥቷል ያሉ ሲሆን በአማካይ አፈፃፀሙ 97.2% በመሆን ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በፍትሀብሔር ጉዳዮች የሚሰጥ ፍርድ ማስፈፀምን በተመለከተ ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው ላይ 63,113,560.34 ብር የሆነ በዓይነት እና በገንዘብ የሚተመን በፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎባቸው ለፍርድ ባለመብቶች እንዲወሰን በማድረግ ከተወሰነው ውሳኔ ውስጥ 49,698,486.87 ብር አፈፃፀሙ (78.7%) በመሆን ለፍርድ ባለመብቶች እንዲከፈል ተደርጓል ሲሉ በሪፖርታቸው ላይ አቅርበዋል፡፡

ከሰብዓዊ መብት ማስከበር ጋር በተያያዘ በበጀት ዓመቱ ውስጥ ለ22,278 በማረፊያ ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን እና ታራሚዎችን ጉብኝት በማድረግ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል ያሉ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ላይ አያይዘውም በተያዙና በተከሰሱ ሰዎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርገዋል ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 12,515 ተገልጋዮች አገልግሎት ጠይቀው ለ12,475(99.7%) አገልግሎት ጠያቂዎች አገልግሎቱን በዜጎች ቻርተር በተቀመጠው መስፈርት መሠረት ምላሽ መስጠት ተችሏል ያሉ ሲሆን፣ አያይዘውም በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 1,100 አቤቱታዎች ቀርበው ለ1,066 አቤቱታዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን አፈፃፀሙ 96.9% በማድረስ ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉን በሪፖርታቸው ላይ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ በቀረበው ሪፖርትም በበጀት ዓመቱ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የእቅድ አፈፃፀም ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችን፣ ውስንነቶችን እና እያጋጠሙ የነበሩ ችግሮችን የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ያነሱ ሲሆን የተነሱትን ጥያቄዎችንና አስተያየቶችንም ዳይሬክተሩ ተገቢውን ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማሰቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: attorney Attorney General Branch Offices Budget budget year case case files citizen charter complaint resolution court decisions criminal Criminal Investigation files Financial Accountability general human rights monitoring Implementation Investigation Justice System monitoring directorate office office of the attorney general performance Performance Evaluation Performance Report plan plan implementation report year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች