በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ይህን ያሉት “የምትተክል ሀገር የሚፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የክረምት በጎ አድራጎትና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተከትሎ ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተዘጋጀ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ነው።
የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ2016 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትና የአርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተገኝተዉ አካሂደዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታዎች፣የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣የተቋማቱ ባለሙያዎች፣የግብረ ሰናይ ድርጅት ተወካዮች፣ተማሪዎች እና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከመደበኛ ተግባራቶቻቸዉ ባሻገር ባለፉት አመታት አመራሮችንና ሰራተኞቻቸዉን በማስተባበር አበረታችና አመርቂ የበጎ አደራጎት ተግባራትን ማከናወኑን አስታዉሰዉ በዘንድሮዉ የክረምት በጎ አድራጎት ስራም እንዲሁም በአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በማካሄድ በክልሉ የድርሻቸዉን ለመወጣት መገኘታቸዉንና ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የከተማ መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተንኳይ ጆክ ሮም በበኩላቸዉ የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋምቤላ ክልል በመገኘት ለሚያከናዉኑት የበጎ አድራጎት ስራ በክልሉ ስም ያላቸዉን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በተለይም ለወጣቶች ባስተላለፉት የማነቃቂያ ንግግር ወጣቶች የስራ ባህልን በማዳበር፣በበጎ ስራ ላይ በመሰማራትና በሰላም ግንባታ ላይ በንቃት በመሳተፍ ሁለንተናዊና ሁሉን አቀፍ ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም በአብሮነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በተመረጡ አካባቢዎች የከተማ ፅዳት የተከናወነ ሲሆን ቀጥሎም በአረንጓዴ አሻራ ከአስር ሺህ የሚበለጡ አስራ አንድ አይነት ዝርያ ያላቸውን ችግኞች በተዘጋጀላቸው ቦታ ተክለዋል።
ቀጥሎም የአምስት አቅመ ደካማ ዜጎች ደረጃውን የጠበቀ የቤት ግንባታ የማስጀመር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 726 ተማሪዎችም የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በቀጣይም የልማት ስራዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የተከሏቸውን ችግኞች የደረሱበትን ደረጃ የማየትና የመንከባከብ እንዲሁም የቤቶቹን ግንባታ የመከታተል ሀላፊነቱን ከመወጣት በተጨማሪ ለአቅመ ደካሞች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልፆል።
የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ባለፋት አመታት ባካሄዷቸው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በአዲስ አበባ፣በኦሮሚያ ክልል በአሌልቱ፣በቢሾፍቱና ዝዋይ፣በአማራ ክልል በሞጣ በሰሜን ሸዋና አሳግርት ፣በሸዋሮቢት እንዲሁም በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ተገኝተው ውጤታማ የሆነ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ፈፅመዋል።
የፌዴራል ማረሚያ ፖሊስ ፣የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ አገልግሎት ፣ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እና የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰበ ድርጅቶች ባለሥልጣን የፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡