የፍትሕ ሚኒስቴር የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድን አስመልክቶ ከክልል ፍትሕ ቢሮ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ምክክር ተደረገ

A Consultation was Held with Heads of Regional Justice Bureaus and Attorney General Institutions Regarding the Ministry of Justice's Five-Year Strategic Plan

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከ2018 እስከ 2022 ዓ.ም የሚዘልቅ የዓምስት ዓመት ስትራቴጂን አስመልክቶ የፍትሕ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ እና ክቡራን ሚኒስትር ዲኤታዎች በተገኙበት ከክልል ፍትሕ ቢሮ እና የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ምክክር ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት ስትራቴጂ ሰነዱን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ባለፉት ወራት በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸው የተገለፀ ሲሆን በዋናነት በቀጣይ ዓመታት ምን ምን ጉዮች ላይ ትኩረት ቢደረግ በፍትሕ ዘርፉ ሰፊ እና ውጤታማ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይቻላል? የሚለው ጉዳይ በትኩረት ሲሰራበት መቆየቱ ተገልፆል።

ስትራቴጂው ውጤታማ እንዲሆን አሳታፊነት ወሳኝ መሆኑን በማመን ከዝግጅቱ ጀምሮ ሁሉን አካታች እንዲሆን ታስቦ ብዙ ዳሰሳዎችን ያካተተና ሰፊ ምክክር የተደረገበት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከፍትሕ ዘርፍ አካላት እና ከክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በሕብረት ተቀናጅቶና ተደጋግፎ መስራትም የስትራቴጂው ቁልፍ ዕሴት መሆኑ ተመላክቷል።

የፍትሕ ሚኒስቴር ስትራቴጂ ለፍትሕ አዲስ መሠረት በሚል የተሻሻለ የፍትሕ አገልግሎት፤የተጠናከረ የሕግ የበላይነት፤ የተሻሻለ ማረምና ማነፅ፤ ያደገ ተቋማዊ ዓቅም እና የተጠናከረ ትብብር እና ቅንጅት በሚሉ አምስት ዋና ዋና አምዶች ስር የተካተቱ በርካታ የስትራቴጂክ እርሞጃዎች ተካተውበት የተዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂው ወደ ትግበራ ምዕራፍ መሸጋገሩ ተጠቁሟል።

በምክክሩ የተሳተፉ ክልሎችም ስትራቴጂ ሲያዘጋጁ በዋናነት የስትራቴጂ ዝግጅት ሂደት ምን መምሰል እንዳለበት፣ የመነሻ ዳሰሳ ሲደረግ በተቻለ መጠን ያሉትን ችግሮች በደንብ መለየት ላይ ማተኮር አስፈላጊ መሆኑንና በቀጣይ ዓመታት ምን እናድርግ የሚለው ላይ ግልፅ በሆነና ለስራ በሚያነሳሳ መልኩ ሊያዘጋጁ እንደሚገባቸው እና በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ አመታዊ ዕቅዳቸውን በስትራቴጂው መሰረት በመከለስ ወደ ተግባር እንዲገቡ በክብርት ሚኒስትሯ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው ምክክሩ በተለይም ስትራቴጂ እያዘጋጁ ባሉበት ጊዜ መካሄዱ ወቅቱን የጠበቀና እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና የተሻለና ተናባቢ ዕቅድ ለማዘጋጀት እንደሚያግዛቸው ገልፀው ድጋፍና እገዛ የሚፈልጉባቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።

በተያያዘም በምክክር መድረኩ በድሬዳዋ በተካሄደው 8ኛው የፍትሕ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ አቅጣጫ የተሰጠባቸው ጉዳዮች አፈፃፀም እና የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት የግንኙነት ሥርዓት አጭር መነሻ ሐሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child attorney Attorney General bureau bureaus Consultation five-year general heads institution institutions itu Justice justice bureau legal counsel ministry ministry of trade and regional integration plan rate rea region Regional Regional justice Regional Justice Bureaus strategic strategic plan year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች